መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 25፣2012-የብስራት ማለዳ አጫጭር መረጃዎች በአሜሪካ ተቃዉሞ ዙሪያ

~ በጥቁር አሜሪካዊዉ ጆርጅ ፍሎይድ በአንድ ነጭ የፖሊስ አባል የግፍ ተግባር ህይወቱን እንዲያጣ መደረጉን ተከትሎ በሀገረ አሜሪካ የተለያዩ ግዛቶችና ከተሞች ተቃዉሞ ቀጥሏል፡፡በዲሲ እና በአትላንታ ከተማ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ፖሊስ ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ መተኮሱ ተሰምቷል፡፡

~ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጋዝ መተኮሱን የዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ከንቲባ ሙሪየል ቦውሰር አሳፋሪ ተግባር ሲሉ ፖሊስን ተችተዋል፡፡

~ የዲሞክራቶች ፕሬዝዳንታዊ እጩ ጆ ባይደን ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ህዝብ ላይ የአሜሪካ ጦር እንዲነሳ አድርገዋል ሲሉ በቲዉተር ገጻቸዉ ላይ ወቀሱ፡፡

~ በአሜሪካ ተቃዉሞ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ቢያንስ 5‚600 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡በጆርጅ ፍሎይድ ላይ የተፈጸመዉን ግፍ ለማዉገዝ አደባባይ ከወጡ ሰዎች መካከል 900 በሎስ አንጀለስ፣800 በኒዉ ዮርክ በሚኒያፖሊስ 155 ሰዎች እና ተጨማሪ በሎሎች የአሜሪካ ከተሞች መታሰራቸዉን የፖሊስ ኤጀንሲ አስታዉቋል፡፡

~ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪክ የአሜሪካ መሪዎችና ባለስልጣናት ለተቃዉሞ የወጡ ዜጎቻቸዉን ሊሰሙ ይገባል ሲሉ ተናገሩ፡፡

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *