መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 27፣2012-በሚኒሶታ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደ ጥናት የጸረ ወባ መድሃኒት የሆነዉ ሀይድሮክሲክሎሮኪዉን የኮሮና ቫይረስን እንደማይከላከል ይፋ ተደረገ

በሚኒሶታ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ክፍል 821 ለቫይረሱ የተጋለጡ ሰዎችን ባሳተፈ መልኩ የተካሄደዉ ጥናት መድሃኒቱ የመከላከል አቅም እንደሌለዉ አረጋግጧል፡፡እነዚህ 821 ሰዎች ቫይረሱ ካለባቸዉ ሰዎች ጋር በቀረበ ሁኔታ የሚሰሩ ሲሆን ይህ የጸረ ወባ መድሃኒት የመከላክል አቅም እንዳልጨመረላቸዉ ዩኒቨርሲቲዉ በጥናቱ ገልጿል፡፡

በተደጋጋሚ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቫይረሱን ለመከላከል የጸረ ወባ መድሃኒት የሆነዉ ሀይድሮክሲክሎሮኪዉን እንደሚጠቀሙ ሲናገሩ ነበር፡፡በተመሳሳይ የብራዚሉ ፕሬዝዳንት ቦርሴናሮ ለወላጅ እናታቸዉ መድሃኒቱን ስለመግዛታቸዉ መናገራቸዉ ይታወሳል፡፡

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *