መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 27፣2012-ከአሜሪካ የተሰሙ አጫጭር መረጃዎች ክፍል 1

~ የቀድሞ የአሜሪካ የመከላከያ ዋና ጸሀፊ ጀምስ ማቲስ ትራምፕ የተፈጠረዉን ቀዉስ በሚገባ መቆጣጠር አልቻሉም፣ ትራምፕ ሊከፋፍሉን ይፈልጋሉ ሲሉ መዉቀሳቸዉን ተከትሎ ትራምፕ በቲዉተር ምላሽ ሰጡ ፤በምላሻቸዉ እኔና ባራክ ኦባማ የሚያመሳስለን ብቸኛ ነገር ቢኖር ማቲስን ከስራ ማሰናበታችን ነዉ ብለዋል፡፡ትጽል ስሙ ብጥብጥ ነበረ ሲሉ ተናገረዋል፡፡

~ በቀጠለዉ ተቃዉሞ ከ10 ሺ በላይ ሰዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰማ፡፡ከጆርጅ ፍሎይድ ህልፈት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ተቃዉሞ መደረጉ የቀጠለ ሲሆን በሎስ አንጀለስ ብቻ በእስር ላይ ለሚገኙ 3ሺ ሰዎች ከ2 ሚሊየን በላይ የአሜሪካ ዶላር ለማሰባሰብ ዘመቻ ተከፍቷል፡፡

~ የሎስ አንጀለስና ሳንፍራንሲስኮ ከተሞች በሀገሪቱ የቀጠለዉን ተቃዉሞ ለማስቆም የጣሉትን የሰዓት እላፊ ሊያነሱ ነወቁ፡የሎስ አንጀለስ ከተማ ከንቲባ ሎንደን ብሪድ የሰዓት እላፊዎ ዛሬ ከ11 ሰዓት ጀምሮ ይነሳል ብላች፡፡

~ በሰሜናዊ ካሮላይና የሚገኝ ፖሊስ ሰልፈኞችን ለመበተን ኬሚካል ያለበትን ሳጥን ወደ ሰልፈኞች በማዞር ለመበተን ሲሞክር የሚያሳይ ቪዲዮ በማህበራዊ ገጽ ትስስር የተጋራ ሲሆን የፖሊሱ ድርጊት ቁጣን ቀስቅሷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *