መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 28፣2012-የፊሊፒንስ ፕሬዝዳንት ዱተርቴ ከፍተኛ መጠን ያለዉ የአደንዛዥ እጽ በሀገሪቱ መያዙን ተከትሎ አዘዋሪዎች ላይ ግድያ መፈጸም አለበት ሲሉ በድጋሚ ማስፈራራት መጀመራቸዉ ተሰማ

ለአደንዛዥ እጽ አዘዋዋሩዎች ምህረት የለሽ የሚባሉት ፕሬዝዳንት ሮድሪጎ ዱተርቴ ስልጣን ከያዙ ከ2016 አንስቶ 5‚600 የአደንዛዥ እጽ ተጠቃሚዎችና አዘዋዋሪዎች በፖሊስ እንዲገደሉ ምክንያት ሆኗል፡፡በሜክሲኮ የሚገኙ የወንጀል ቡድኖች የወንጀል ቡድኖች የአደንዛዥ እጽ መዳረሻ ፊሊፒንስ ናት፡፡

102 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር የሚያወጣ 75 ኪ.ግ የሚመዝን አደንዛዥ እጽ በሀገሪቱ መገኘቱን ተከትሎ ዱተርቴ በመልዕክታቸዉ እንዳስተላለፉት በአድንዛ እጽ ፊሊፒንስን የምታጠፉ ከሆነ እገድላችኃለሁ ሲሉ ዝተዋል፡፡

ፕሬዝዳንት በአዘዋዋሪዎችና በተጠቃሚዎች ላይ ግድያ እንዲፈጸም ማዘዛቸዉን የሚተቹ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጆሮ የማይሰጡ ሲሆን ድርጊታቸዉን አጠናክረዉ ቀጥለዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *