መደበኛ ያልሆነ

ግንቦት 29፣2012-በሶርያ በተሸከርካሪ ላይ የተጠመደ ቦምብ ፈንድቶ የስምንት ሰዎች ህይወት አለፈ

በሰሜን ምስራቃዊ ሶርያ ሀሳካ ግዛት በተሽከርካሪ ላይ የተጠመደ ቦምብ ፈንድቶ የስምንት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች መቁሰላቸዉን የሶርያ የዜና ኤጀንሲ ሳና ዘግቧል፡፡አካባቢዉ በቱርክ ጦር ስር የሚገኝ ሲሆን በመኪና ላይ የተጠመደዉ ቦምብ ባስከተለዉ ከባድ ፍንዳት ሌሎች ተሸከርካሪዎች ላይ ጉዳት በማድረስ ንጹሃን ተጎጂ እንዲሆኑ ምክንያት ሆኗል፡፡

ለጥቃቱ እስካሁን ድረስ ሀላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም ቱርክ ግን ጣቷን በከርዲስታን ፓርቲ(YPG) ላይ ቀስራለች፡፡ከፒኬኬ ጋር ህብረት ያለዉ የዋይ ፒ ጂ ቡድን ከዋሽንግተን አስተዳደር ድጋፍ ያገኛል፡፡

ይህ ቡድን እ.ኤአ. ከ1984 አንስቶ ደቡብ ምስራቃዊ ቱርክን በመገንጠል ነጻ የኩርዶች ምድር ለመመስረት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *