መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 2፣2012-የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ባለፈዉ ዓመት በዉሃን ከተማ ነሀሴ ወር ላይ መቀስቀሱን የሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ይፋ ቢያደርግም ቻይና ከእዉነት የራቀ ስትል መረጃዉን አጣጣለች

የሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ከሳተላይት በተገኘ መረጃ መሰረት ቫይረሱ ባለፈዉ 2019 ዓመት በነሀሴ ወር መቀስቀሱን ይፋ ቢያደርግም ቻይና ሪፖርቱ የፌዝ መረጃ ነዉ ስትል አስተባብላለች፡፡የሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ እንደሚለዉ ቫይረሱ ባለፈዉ ዓመት ነሀሴ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተቀሰቀሰ በኃላ በታህሳስ ወር መስፋፋቱን በሆስፒታል የመኪና ማቆሚያ ስፍራ የተገኘዉ የሳተላይት ምስል ያሳያል ብሏል፡፡

በዉሃን ከተማ ሆስፒታል የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች በከፍተኛ ደረጃ መጨናነቅ የጀመሩት ካለፈዉ ዓመት ነሀሴ ወር ጀምሮ ስለመሆኑ የሀርቫርድ ጥናት ያመላክታል፡፡የቻይና የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ የሆነችዉ ቹይንግ መረጃዉን አስተባብላለች፡፡

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *