መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 4፣2012-በህንድ ከቤት መውጣት የሚከለክለው መመሪያ ማብቃቱን በማስመልከት በተዘጋጀ ግብዣ ላይ የታደሙ 180 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

በህንድ ናግፑር ከተማ እንቅስቃሴ የሚከለክለው መመሪያ ማብቃቱን ተከትሎ አንድ ግለሰብ ባዘጋጀው ግብዣ ላይ የተገኙ 180 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ተሰምቷል።ለግብዣው ስጋ ለመግዛት ከአምስት ጓደኞቹ ጋር ያቀናው የግብዣው አዘጋጅ ስጋ የገዛባት አውራጃ በርካታ የቫይረሱ ተጠቂዎች የተለዩባት ስፍራ ነበረች።በዚሁ ስፍራ በቫይረሱ ሳይጠቁ እንዳልቀሩ ተግልጻል።

የናግፑር ከተማ ኮሚሽነር ቱካርማ መድሂ እንደተናገሩት በግብዣው ላይ ታድመው በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጠው 180 ሰዎች መካከል 16ቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው ብለዋል።ከህሙማኑ ጋር ንኪኪ ነበራቸው የተባሉ 700 ሰዎች ወደ ለይቶ ማቆያ ስለመግባታቸው ተሰምተል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *