መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 4፣2012-በመኪና አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው በትላትናው እለት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ገደማ ነው።

ሁለት የሲኖትራክ ተሸከርካሪዎች እርስ በርስ በመጋጨታቸው የአንድ ሰው ህይወት ሊያልፍ መቻሉን በአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

በሌላ ዜና በክፍለ ከተማው ወረዳ 11 ከለሊቱ ሰባት ሰዓት በሱቆች ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ፤ ሁለት ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል ተብሏል።

የእሳት አደጋው በኤክትሪክ ኮንታክት አልያም ንክኪ የተፈጠረ ሲሆን ፤ አንድ ሺ ካሬ ሜትር መሸፈኑም ታውቋል፡፡

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከአዲስአበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን ባደረገው ጥረት ፤ ከአደጋዎቹ 6 ሚሊየን የሚገመት ንብረት ማትረፍ ሲቻል ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ንብረት መውደሙን አቶ ጉልላት ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *