መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 4፣2012-በኢንዶኔዥያ ባል ሚስቱን ካገባት ከሁለት ቀናት በኃላ ወንድ ሆኖ በመገኘቱ ፍቺ ፈጸመ

የኢንዶኔዥያ ዜግነት ያለዉ ሙሃ የተባለ ግለሰብ ከ25 ዓመቷ ሚታ ጋር በኦንላይን አማካይነት ይተዋወቃሉ፡፡ይህ ትዉዉቃቸዉ በድህረ ገጽ ከመሆኑ በላይ በአካል በመገናኘት ጥሩ ጊዜን በጋራ ማሳለፋቸዉን ሙሃ ይናገራል፡፡ታዲያ በጋራ በነበሩበት ጊዜ ሚታ በተደጋጋሚ ጥሎሽ ጥሎ በኢንዶኔዝያ ደንብ አግባኝ የሚል ጥያቄን ታቀርባለች፡፡

ይህንኑ ጥያቄ ለቤተሰቦቹ በማሳወቅ ሙሃ ከቤተሰቡና ከራሱ ያሰባሰበዉን 20 ሚሊየን የኢንዶኔዥያ ሩፒ በማዉጣት ጥሎሽ ጥሎ ደግሶ ይገባሉ፡፡ከትዳር በኃላ ግን ነገሩ እንደጠበቀዉ በፍቅር የሚቀጥል ሊሆን አልቻለም፡፡በሁኔታዉ ግራ የተጋባዉ ሙሃ መታለሉን ሴት ሳይሆን ወንድ ማግባቱን ቆይቶ ይረዳል፡፡

በሰርጉ እለት በኢንዶኔዥያ ደንብ ሙሽሪት በመሸፋፈኗ ቤተሰብና እድምተኛ ባይገነዘብም እንዴት እርሱ አብረዉ ሲያሳልፉ ሊለየዉ አልቻለም የሚል ጥያቄን አስነስቷል፡፡ፖሊስ የ25 ዓመቷን ሚታ በትክክለኛዉ ስሙ አዲ የተባለዉን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አዉሏል፡፡በኢንዶኔዥያ ምድር ፈጣኑ ፍቺ ተብሏል፡፡

በያዝነዉ ዓመት በዩጋንዳ አንድ ግለሰብ በሰርግ ያገቧት ሚስታቸዉ ወንድ ሆኖ ከሁለት ሳምንተ በኃላ መገኘቱ መነገሩ አይዘነጋም፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *