መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 4፣2012-በኬንያ አንዲት ሴት በሞተር ሳይክል ጎትተዋል የተባሉ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ

ሶስት የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ከሶስቱ አንዳቸዉ አንዲት ግለሰብን በሞተር ሳይክል መሬት ለመሬት መጎተታቸዉን የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ድህረ ገጽ መሰራጨቱን ተከትሎ ነዉ፡፡በናኩሪ ግዛት ከተፈጸመ ወንጀል ጋር ግለሰቧ በዝርፊያ ላይ ተሰማርለች በሚል ድርጊቱ በፖሊስ ተፈጽሟል፡፡

የወንጀል ምርመራ ቢሮ ተጨማሪ የማጣራት ስራዎችን ለማከናዉን ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር አዉሏል፡፡በዚህ መልኩ ጥቃት የደረሰባት ግለሰብ በእጅና እግሮቿ ላይ ባጋጠማት ጉዳት ወደ ሆስፒታል እንድትገባ መድረጉ ተነግሯል፡፡

በኬንያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 15 ሰዎች በፖሊስ መገደላቸዉ ሪፖርት ሲደረግ 31 ሰዎች ክፉኛ ቆስለዋል፡፡የሰብዓዊ መብት ተቋማት ድርጊቱን በማዉገዝ ላይ ይገኛሉ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *