መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 4፣2012-የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የምረጡኝ ዘመቻቸውን በቀጣዩ ሳምንት እንደሚጀምሩ አስታወቁ፡፡

በቀጣዩ ሳምንት አርብ ለ 2020 የአሜሪካ ምርጫ የምረጡኝ ዘመቻ በኦክላሆማ ግዛት ይጀምራሉ፡፡

ትራምፕ በወርሃ ህዳር ለሚካሄደው ምርጫ በድጋሚ እንደሚያሸንፉ ተስፋ እያደረጉ ቢሆንም ከህዝብ የተሰበሰበው ድምፅ ለተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን ያጋደሉ ሆነዋል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ምላሽ ዙሪያ ፣ በጥቁሮች የመብት ረገጣ ረገድ ትራምፕ ነጥብ እንደጣሉ በስፋት እየተነገረ ይገኛል፡፡

የቫይረሱ ስርጭት ከፖለቲካ ውጥረቱ አንፃር ከባድ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *