መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 5፣2012-ኬንያ የብሩንዲ ፕሬዝዳንት ህልፈት ተከትሎ ከነገ ጀምሮ ሰንደቋ ዝቅ ብሎ እንዲዉለበለብ ወሰነች

የኬንያዉ ፕሬዝዳንት ኧሁሩ ኬንያታ በዛሬዉ እለት እንዳስታወቁት የብሩንዲዉ ፕሬዝዳንት ፔየሪ ኒኩሪንዚዛ ህልፈትን ተከትሎ የሀገሪቱ ሰንደቅ አላማ ከነገ ጀምሮ የቀብር ስነስርዓቱ እስኪፈጸም ድረስ ዝቅ ብሎ እንዲዉለበለብ ዉሳኔ መተላለፉን አሳዉቀዋል፡፡

ስታር የተሰኘ ጋዜጣ ከዲፕሎማት ምንጮቼ አገኘሁት ባለዉ መረጃ መሰረት የብሩንዲዉ ፕሬዝዳንት ከህልፈታቸዉ በፊት በኬንያ መዲና ናይሮቢ አልያም በታንዛኒያ የንግድ ማዕከል ዳሬሰላም ከተማ ህክምና ሳያደርጉ እንዳልቀረ ጽፏል፡፡

የሟች ፕሬዝዳንቱ ባለቤት ዴኒስ ኒኩሪንዚዛ የባላቸዉን ህልፈት የሰሙት በናይሮቢ ሆስፒታል እየታከሙ በነበረበት ጊዜ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *