መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 5፣2012-2.2 ሚሊየን ብር የምታወጣዋ ሀይሉክስ ቶዮታ ተሸከርካሪ ዳውሮ ዞን ለሚገኘው የመንግስት ሰራተኛ ደረሰች

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ገቢ ለማሰባሰብ የሚካሄደው የ8100 A 3ኛ ዙር ዕጣ የሆነችው የ2.2 ሚሊየን ብር ሀይሉክስ ቶዮታ ተሸከርካሪ ዳሮ ዞን ለሚገኝ የመንግስት ሰራተኛ በዛሬው እለት መውጣቱን የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ አስተባባሪ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ዕጣው የካቲት 25 ቀን 2012 በታለቁ ቤተመንግስት በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው እለት መውጣቱ ተነግሯል፡፡

በሶስት ወር 18 ሚሊየን ብር የሰበሰበው የሶስተኛው ዙሪ 8100 እጣ በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ በተካሄደ የዕጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት አሸናፊው ቁጥር 17618387 ሆኖ መውጣቱን የጽህፈት ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሀይሉ አብረሀም ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

አሁን የወጣው ሶስተኛው ዙር ሲሆን የመጀመሪያው ዙር 2007 ዓ.ም የነበረ ሲሆን በወቅቱ 80 ሚሊየን ብር መሰብሰብ ተችሏል፡፡ በሁለተኛው ዙር በ2008 የተካሄደ ሲሆን 49 ሚሊየን ብር በወቅቱ መገኘቱን ከጽህፈት ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ብስራት ሬድዮ ዳውሮ ዞን ለሚገኘው ባእድል አቶ አብረሀም ሀሌኮ በነበረው የስልክ ቆይታ አቶ አብረሀም የአራት ልጆች አባት ሲሆን በቀርጫ የጤና ጣቢያ የጤና ባለሙያ መሆኑን ተናግሯል፡፡

በ8100 በስልክ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያው ለተጨማሪ ሶስት ወር የሚቆይ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *