መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 5፣2012-በኮሮና ቫይረስ ቀውስ የተነሳ በከፋ ድህነት ውስጥ የሚገኘው የአለም ህዝብ ወደ 1.1 ቢሊየን ከፍ ሊል እንደሚችል ተጠቆመ

የኮሮና ቫይረስ ባስከተለው ከፍተኛ የኢኮኖሚ ኪሳራ የተነሳ ተጨማሪ 395 ሚሊየን የአለም ህዝብ ለከፋ ድህነት ሊጋለጥ እንደሚችል ተጠቁሟል።ይህንኑ ተከትሎ አጠቃላይ በከፋ ድህነት ውስጥ የሚገኘው ህዝብ ብዛት 1.1 ቢሊየን ሊደርስ እንደሚችል በመንግስታቱ ድርጅት ዩኒቨርሲቲ የአለም የኢኮኖሚ ልማት ኢንስቲትዩት ይፋ አድርጓል።

የከፈ ድህነት በሚል በመንግስታቱ ድርጅት የተቀመጠው መስፈርት የእለት ገቢ ከ1.9 የአሜሪካ ዶላር በታች ነው።የኮሮና ቀውስ በመንግስታቱ ድርጅት የተያዘውን ድህነትን ከዓለም የማጥፋት ግብ ላይ ጫና ሊያሳድር እንደሚችል ተገምቷል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *