መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 6፣2012-በአዲስ አበባ ሕገወጥ እርድ ያከናወኑ 132 ልኳንዳ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ

በህገወጥ መንገድ የታረደ የ50 ከብት ስጋ እና ከ360 በላይ የበግ እና የፍየል ስጋ በቁጥጥር ስር መዋሉንና በ132 ልኳንዳ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ገልጿል፡፡

የተወሰኑ ስጋ ቤቶች አንድ በሬ በቄራዎች ድርጅት እርድ ካከናወኑ በኋላ በዚህ ሽፋን ተጨማሪ በሬዎችን ከቄራዎች ድርጅት እንደታረዱ በማስመሰል ህገወጥ ስጋ ለህብረተሰቡ ሊሸጡ መገኘታቸውን ተጠቁሟል፡፡

በዚህ ተግባር የተሳተፉ በርካታ ግለሰቦች እና የልኳንዳ ቤት ባለንብረቶች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *