መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 6፣2012-አጫጭር መረጃዎች የጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ጋር በተያያዘ

~ በፈረንሳይ በማዕከላዊ ፓሪስ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የጆርጅ ፍሎይድን ግድያና ዘረኝነትን ተቃዉመዋል፡፡ፖሊስ የሀይል እርምጃን ከመዉሰድ እንዲቆጠብ ሰልፈኞች ጠይቀዋል፡፡

~ ፍትህ ከሌለ ሰላም የለም በሚል መርህ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች በአዉስትራሊያ የተለያዩ ከተሞች በፍሎይድ ግድያ ዙርያ ተቃዉሞ አሰምተዋል፡፡በአዉስትራሊያ አጠቃላይ የጥቁሮች ብዛት ከአዉስትራሊያ ህዝብ 3.3 በመቶ ድርሻ ቢኖረዉም በመላዉ አዉስትራሊያ ማረሚያ ቤቶች ዉስጥ 27 በመቶ ጥቁሮች ይገኛሉ፡፡

~ የቀኝ ዘመሞች እና የጸረ ዘረኝነት ተቃዋሚዎች በእንግሊዝ ለንደን በዛሬዉ እለት ተቃዉሞ አሰምተዋል፡፡የዊንስተን ቸርችል ሀዉልት የመጤ ጠል ምልክት ነዉ ሲሉ ሰልፈኞች ተቃዉሞ አሰምተዋል፡፡

~ ሲኤንኤን የነጮች የበላይነትን በሚገባ የፈተሸ በጥቁሮች ላይ የሚደርሰዉን ተጽእኖ ያሳዩ ፊልሞችን ይፋ አድርጓል፡፡በእረፍት ቀናችሁ ለመመልከት እንዲያመቻችሁ ርዕሱን እንነገራችሁ፡፡”Harriet” (2019) ፣ “Rosewood” (1997) ፣ “Selma” (2014) ፣ “Boyz N The Hood” (1991) ፣ Queen and Slim”

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *