መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 6፣2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ በግብጽ ከሁለት ሳምንት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ተመዘገበ፡፡በ24 ሰዓት ዉስጥ 1,577 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ የተጠቂዎች ቁጥር 41ሺ ሲደርስ የ1,422 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

~ በብራዚል በኮሮና ቫይረስ የሟቾች ቁጥር ከዩናይትድ ኪንግደም በለጠ፡፡ብራዚል ከአሜሪካ በመቀጠል በ41,901 ሞት ከአለም 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

~ በኔፓል ለኮሮና ቫይረስ በቂ ምላሽ መንግስት አልሰጠም ያሉ ሰዎች አደባባይ በመዉጣት ተቃዉሞ አሰምተዋል፡፡ፖሊስ በርካቶችን በቁጥጥር ስር አዉሏል፡፡

~ ፈረንሳይ ከሰኞ ጀምሮ ከልክላዉ የነበረዉን የድንበር ጉዞ ከሰኞ ጀምሮ ለአዉሮጳ አባል ሀገራት ትፈቅዳለች፡፡የአየር፣የየብስና የባህር ጉዞ ከሰኞ ጀምሮ ክፍት ይደረጋል፡፡

~ በሜክሲኮ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ፍጥነት በመዛመት ላይ ቢሆንም በመዲናዋ ሜክሲኮ ሲቲ ጨምሮ እንቅስቃሴን የሚከለክለዉ ገደብ በቀጣዩ ሳምንት ይነሳል ተባለ፡፡340ሺ የፋብሪካ ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸዉ ይመለሳሉ፡፡

~ የቻይና መዲና ቤጂንግ ስድስት ሰዎች ላይ በሀገር ዉስጥ በተዛመት የኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉን ተከትሎ የከተማዋን ትልቁን የገበያ ስፍራ ሺፋዲን በጊዜያዊነት ዘጋች፡፡

~ የአሜሪካ የኢንፌክሽን በሽታ መቆጣጠር ሀላፊ ዶ/ር አንቶኒዮ ፋዉቺ እንቅስቃሴ ዳግም በአሜሪካ መመለሱ የተጠቂዎች ቁጥር እንዲጨምር እያደረገ መሆኑን አሳወቁ፡፡በቴክሳስና ሰሜናዊ ካሮላይና ቫይረሱ ከዚህ በፊት ከተመዘገበዉ በላይ በፍጥነት ተዛምቷል፡፡

~ ኢራን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎች የማይከበሩ ከሆነ በድጋሚ እንቅስቃሴን የሚከለክሉ ህጎችን ተግባራዊ ልታደርግ እንደምትችል ፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሃኒ ተናገሩ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *