መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 8፣2012-በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት እንዲታወጅ ጥሪ ያቀረቡት ግብፃዊው ቢሊየነር ሳዋሪስ ማን ናቸው?

~ የቢሊየነሩ አባት ኦኒሊ ሳዋሪስ ከግብፅ ቀደምት ባለሀብቶች ተርታ ይመደባሉ፡፡ እኚህ ሰው የኦራስኮም ግሩፕ ባለቤት ናቸው፡፡

~ግለሰቡ የሶስት ወንድ ልጆች አባት ሲሆኑ ናሲፍ ሳዋሪስ ፣ ሳሚያ ሳዋሪስ እና ናጉብ ሳዋሪስ ይባላል፡፡

~ከልጆቻቸው መካከል እ.ኤ.አ በ 1954 የተወለደውና በዛሬው እለት ደግሞ 66ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን የሚያከብሩት ናጉብ ኦንሲ ሳዋሪስ ማበግብፅ መዲና ካይሮ የተወለዱት ሲሆን ናጉብ ሳዋሪስ በሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ከካይሮ ዩኒቨርሲቲ በዲፕሎማ ተመርቀዋል።እንዲሁም በዙሪክ እና በካይሮ በሚገኘው የጀርመን ኢቫንጃሊካል ት/ቤት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።

~ከሀብታም ቤተሰብ የተገኙት ናጉብ ሳዋሪስ ወንድማቸው ናፊስ ከቢሊየነሮቹ ተርታ ይገኛሉ፡፡

~በቤተሰቡ ኦራስኮም በተባለ ኩባንያ ውስጥ ሳዋሪስ በባቡር ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና በቴሌ ዘርፍ ተሰምርቷል፡፡

~ ፎርብስ ባወጣው መረጃ የተጣራ ሀብቻውን 2.8 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ሲያደርሰው ከዓለም 577ኛ ከአፍሪካ 7ኛው ቱጃሩ ሰው ናቸው ይላል፡፡

~ግብፃዊው ቢሊየነር ናጉን ሳዋሪስ የኮፕቲክ ክርስቲያን ናቸው፡፡ የአራት ልጆች አባት ሲሆን አረብኛ ፣ እንግሊዝኛ ፣ ጀርመንኛ እና ፈረንሳይኛ አቀላጥፈው ይናገኛሉ፡፡

~ኦራስኮም ከተሰኘው ኩባንያ በተጨማሪ በግዙፍ የአውሮፓ የመገናኛ ብዙሃን ኢሮኒውስ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ አላቸው፡፡ በግራናዳ ቅንጡ ሆቴል ገንብተዋል፡፡

~ግብፃዊው ባለሃብት ከግሪክ ወይም ጣሊያን ደሴት በመግዛት ከ 100ሺህ እስከ 200ሺህ ስደተኞችን በደሴቷ መሰረተ ልማት ብፕመገንባት ስደተኞችን ለማስፈር እቅድ እንደነበራቸው አይዘነጋም፡፡ የደሴቲቱም ስም በቱርክ በባህር ዳርቻ ህይወቱ ባለፈው የሶርያ ስደተኛ ኢሊን ለመሰየም ፍላጎት እንደነበራቸው ተናግረው ነበር፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *