መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 8፣2012-ኅብረተሰቡ መጪውን የፀሐይ ግርዶሽ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲመለከት ጥሪ ቀረበ

ኅብረተሰቡ ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም የሚጠበቀውን የፀሐይ ግርዶሽ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንዲመለከት ለማድረግ በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች እና በመገናኛ ብዙኃን በኩል መልእክቶች እያስተላለፈ መሆኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ጥሪ አቅርቧል።

ሶሳይቲው በፌስቡክ ገጹ ባስተላለፈው መልእክት የፀሐይ ግርዶሽ ለማየት ያስችላል፣ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተመስክሮለታል በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዋወቀ የሚገኘው መመልከቻ መነጽር እውቅና እንደሌለው አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲም ሆነ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለየትኛውም ዓይነት የግርዶሽ መመልከቻ መነጽር ማረጋገጫ እውቅና አልሰጡም ብሏል።

እውቅና ለሚሰጣቸው አካላት ሕጋዊ ማረጋገጫ ደብዳቤ የሚይዙ መሆኑን ኅብረተሰቡ ተገንዝቦ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *