መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 8፣2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎችአጫጭር መረጃዎች

~ በኔፓል በለቶ ማቆያ ውስጥ የነበረች ሴት የአስገድዶ መደፈር ጥቃት ደረሰባት።ፖሊስ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ሶስት ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።ግለሰቧ ከህንድ የመጣች ሲሆን የ14 ቀናት መመሪያን በማክበር በለይቶ ማቆያ ትምህርት ቤት ውስጥ ነበረች ተብሏል።

~ በኒውዮርክ እስከ 25 ሰው ሆኖ መሰብሰብ በቅርቡ እንደሚፈቀድ የኒውዮርክ ገዢ አንድሪው ኩሞ አስታውቀዋል።ከአሜሪካ ግዛቶች ክፉኛ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃችው ኒውዮርክ ከእለት ወደ እለት መሻሻል እየታየባት ይገኛል።

~ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ በጋራ መሰብሰብ መመሪያን በመጣስ በተራረማ ስፍራዎች ምዕመናንን የሰበሰቡ ስድስት የሞዛምቢክ የሀይማኖት መሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

~ ግዙፉ የነዳጅ አቅራቢ ተቋም BP ከኮሮና ቫይረስ ቀውስ በኃላ እስከ 2050 የነዳጅ ዋጋ እየቀነሰ እንደሚሄድ አስታወቀ።ኩባንያው ስራ ቀዝቅዞብኛል በሚል 10ሺ ሰራተኞቹን ለመቀነስ እቅድ ይዟል።

~ በዙምባብዌ ታዋቂው የንግድ ሰው ዲሊሽ ኒጉዋያ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ግዢ ጋር በተያያዘ በከፍተኛ የገንዘብ ምዝበራ ውስጥ በመሳተፉ ክስ ቀረበበት።መንግስት የግዢ ውል ስምምነቱን ከምዝበራ ጋር በተያያዘ ሰርዟል።

~ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተራዝሞ የነበረው የሰሜናዊ ሜቄዶኒያ ምርጫ በሀምሌ አጋማሽ እንዲካሄድ ፖለቲከኞች ከስምምነት ላይ ደረሱ።በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የስልጣን ዘመን በወርሃ ሚያዚያ አብቅቷል።ሰሜናዊ ሜቄዶኒያ ከሁለት ሚሊየን የበለጠ ህዝብ ባይኖርባትም ከ4ሺ በላይ የቫይረሱ ተጠቂዎችና 200 የሚጠጋ ሞት ተመዝግቦባታል።

~ በሲንጋፖር ከአርብ ጀምሮ የንግድ እንቅስቃሴ ክፍት ይደረጋል ተባለ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *