መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 10፤2012-በሀረር ከተማ የ8ወር ነብሰ ጡር በኤሌክትሪክ ህይወቷ አለፈ

በሀረር ከተማ አሚር ኑር ወረዳ ቀበሌ 01 ውስጥ አንዲት የ27 አመት ወጣት የ8ወር ነብሰ ጡር በኤሌክትሪክ ህይወቷ ማለፉን የወንጀል ምርመራ ምክትል ዳሬክተር የሆኑት ዋና ኢንስፔክተር አብዲ ቶፊቅ ገልፀዋል።

ወጣት ሙስጠቂማ የሱፍ የተባለች በዚሁ ወረዳ ነዋሪ ስትሆን በአካባቢዋ ለቅሶ ደርሳ ስትመለስ የዋናው የኤሌትሪክ ፖልና ገመዱ ወድቆ ስለነበር ወጣትዋ በመጓዝ ላይ እያለች የተበጠሰው የኤሌትሪክ ገመድ ይዟት ህይወቷ አልፏል።

አደጋ እንዳይደርስና ፈጥነው የኤሌትሪክ ሀይሉን እንዲያቋርጡ ከፖሊስ መረጃ በተደጋጋሚ ተደውሎ እንደነበር ከዚህም ውጪ በአካባቢው ሰው ተደውሎ እንዳልመጡ ምላሽም እንዳልሰጡ ዋና ኢንስፔክተር አብዲ ገልፀዋል።

ፖሊስ እንደሚገልፀው አደጋ በሚደርስበት ወቅት እንዲሁም መብራት ሲቋረጥ በተደጋጋሚ ጥሪ ቢደረግላቸውም ለጥሪው ምላሽ እንደማይሰጡ ቅሬታውን ገልፆል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *