መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 10፤2012-በፍቼ ከተማ የ15 ዓመቱ ታዳጊ በብስክሌት የ29 ዓመቱን ወጣት በመግጨቱ የወጣቱ ህይወት አለፈ

በፍቼ ከተማ 03 ቀበሌ መናሃሪያ አካባቢ የ15 ዓመቱ ታዳጊ ዋቅሹም ፍቅሬ የተከራየውን ብስክሌት ፍጥነት መቆጣጠር ተስኖት ወደ ገበያ የወጣውን የሶስት ልጆች አባት የ29 ዓመቱ አቶ ሰለሞን ደምሴን በመግጨቱ ህይወቱ አልፏል።

የ4ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ታዳጊ በአደጋው ተጎጂ የነበረ ሲሆን በቸልተኝነት በፈፀመው ወንጀል በወጣት ጥፋተኛ ተጠያቂ እንደሚሆን የፍቼ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ፈይሳ ቶላ ተናግረዋል።

ታዳጊ ወጣቶች በድንገት በሚፈጠር መሰል ክስተት ለስነልቦና ሆነ ለአካላዊ ጉድት እንዳይዳረጉ ወላጆች ሆኑ አሳዳጊዎች ግዜውን ከግምት በማስገባት ክትትል እንዳይለያቸው ጥሪ አቅርበዋል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *