መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 10፤2012-አሜሪካ የሳይበር ምዝበራ ፈፅመዋል ያለቻቸውን ስድስት የናይጄሪያ ዜጎች ንብረት እንዳይንቀሳቀስ አገደች

በአሜሪካውያን እና በአነስተኛ ንግድ ባላቸው ዜጎች ላይ ስድስት የናይጄሪያ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በፈፀሙት ምዝበራ 6 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ኪሳራ ደርሷል።ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሩ የተጎጂዎችን ስም፣የይለፍ የሚስጥር ቁጥርና የባንክ ሰነድ በመጠቀም የተፈፀመ ነው።

በብዛት የሳይበር ምዝበራው በሴቶች እና እድሜያቸው ከፍ ባሉ ሰዎች ላይ መፈፀሙ ተነግሯል።ኢሜልና ማህበራዊ ገፅ ትስስርን በመጠቀም የተፈፀመ ድርጊት ሲሆን በቴክኖሎጂ በመጠቀም አሜሪካውያን ተጎጂ መሆናቸውን የውጪ ጉዳይ ዋና ፀሀፊ ማይክ ፖምፒዮ ተናግረዋል።

በ2019 ነሀሴ ወር በተመሳሳይ 80 የውጪ ዜጎች የበዙት ናይጄሪያውያን ከ46 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ምዝበራ ጋር በተያያዘ ክስ እንደተመሰረተባቸው ይታወሳል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *