መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 10፤2012-የሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር አዲስ አበባ ገብተዋል።

ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንቱ አዲስ አበባ ሲገቡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸውና በጀኔራል አደም መሐመድ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ በቆይታቸው ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሀገራቱ ግንኙነትና በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *