መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 10፤2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ የእስራኤል ሳይንቲስቶች ራሱን በራሱ የሚያፀዳና የኮሮና ቫይረስን የመግደል አቅም ያለው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ(ማስክ)ሰሩ።በሞባይል ቻርጀር ለ30 ደቂቃ ቻርጅ ሲደረግ ማስኩ ራሱን በራሱ ያፀዳል።በአንድ የአሜሪካ ዶላር ለመሸጥ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

~ በአሜሪካ ፍሎሪዳ እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ ባሳለፍነው ዓርብ ለመዝናናት ወደ ፍሎሪዳ ባር ያመሩ 16 ጓደኛማቾች ሁሉም በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋገጠ።

~ በቻይና መዲና ቤጂንግ የጅምላ የንግድ ስፍራ በሆነው ሺፈዳ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች መገኘታቸውን ተከትሎ ቤጂንግ በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ ለ356ሺ ሰዎች ምርመራ አደረገች።የቤጂንግ ከተማ በቀን ለ400ሺ ሰዎች ምርመራ የማድረግ አቅም አላት።

~ ጀርመን እስከ ወርሃ ጥቅምት ድረስ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው የሚሳተፍበትን ስብሰባን እና ዝግጅቶችን ማዛጋጀት እንደማይቻል አስታወቀች።

~ የቴክሳስ ግዛት ገዢ ግሪግ አቦት በግዛቲቱ የኮሮና ቫይረስ በድጋሚ የተሰራጨው ወጣቶች ወደ መዝናኛ ስፍራ በማዝወተራቸው የተነሳ ነው ሲሉ ተችተዋል።

~ በመላው አለም ካለው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች የአፍሪካ ሀገራት ድርሻ 3 በመቶ መሆኑ ተጠቆመ።በአፍሪካ ከ76ሺ በላይ የቫይረሱ ተጠቂ ያለባት ግብፅ ቀዳሚ ስትሆን ደቡብ አፍሪካ፣ናይጄሪያና ጋና ይከተላሉ።

~ የደቡብ አፍሪካ ዋንኛ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ጁልየስ ማልማ በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ እንዳይስፋፋ ተጥሎ የነበረው የአልኮል መጠጥ ሽያጭ መነሳት አልነበረበትም ሲሉ ተናገሩ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *