መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 10፤2012-የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ዑማ ከተለያዩ የስፖርት ቤተሰብ አባላት ጋር ችግኝ ተከሉ።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ሲኤምሲ አካባቢ በሚገኝ የስፖርት ማዕከል በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ታዋቂ አትሌቶች፣ የወንድና ሴት የእግር ኳስ ተጫዋቾችና አሠልጣኞች ፤ የእግር ኳስ ደጋፊ ማኅበራት ተሳታፊ ሆነዋል።

የስፖርት ቤተሰቡ ከምክትል ከንቲባው ጋር ያደረጉት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ የሆነውን ኮቪድ 19 በመከላከል ዜጎች ባሉበትና በሚኖሩበት አካባቢ ችግኝ
እንዲተክሉና የተከሉትንም እንዲንከባከቡ ለማነሳሳት ነውም ተብሏል፡፡

የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የሚተከሉ ችግኞች የአዲስ አበባ ከተማን ዉብ እና አረንጓዴ ከማድረግ ባለፈ የነዋሪዎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ መሠረት የሚጥሉ
ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞች ናቸው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ሰባት ሚሊየን ችግኝ ለመትከል እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተሪያት በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *