መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 11፤2012-በአዲስ አበባ የሸማ ጥበብ ማዕከል ግንባታ ተጀመረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በሽሮ ሜዳ የሸማ ጥበብ ማዕከል ግንባታ መጀመሩን ገለጹ።

ምክትል ከንቲባው በፌስ ቡክ ገጻቸው እንዳሰፈሩት ”የአገራችን ጠቢባን እጅ ስራ ግሩም ድንቅ ሆኖ ፈትል ሸምኖ ሲያሞቀን ሲያደምቀን ኖሯል”ብለዋል።

”ጠቢባኑን ግን በሚመቻቸው መንገድ እንዲሰሩ፣ ስራቸው ተስፋፍቶ ሸማቸው አገር ከማልበስ ተሻግሮ ለአገር ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ እንዲያደርግ አልተደረገም”ሲሉ ገልጸዋል።

ስለሆነም በከተማችን ብዙ የሸማ ጥበብ ስራ በሚሰራበት ሽሮ ሜዳ ማዕከል ሆኖ የሚያገለግል ግንባታ ጀምረናልም ነው ያሉት።

ሃላፊው አያዘውም ”ከጥበቡ “ሸማ”ን ከሰፈሩ “ሜዳ”ን ወስደን የወደፊቱን የኢትዮጲያ ጥበብ ማበልፀጊያ ማዕከል “ሸማ ሜዳ”ን በፍጥነት አጠናቀን ለአገልግሎት እናበቃለን” ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *