መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 11፤2012-በፔሩ ያሉ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከጣልያን በለጠ

በአዉሮጳ በኮሮና ቫይረስ ክፉኛ ተጎጂ ከሆነችዉ ሀገር በበለጠ የደቡብ አሜሪካ ሀገር የሆነችዉ ፔሩ በቫይረሱ ተጠቂዎች ብዛት ብልጫ ይዛለች፡፡240,908 የቫይረሱ ተጠቂዎች ባሉባት ፔሩ እስካሁን ድረስ ባለዉ መረጃ የ7,257 የቫይረሱ ተጠቂዎች ህይወት አልፏል፡፡

ፔሩ በአማካይ በቀን ከ3500 በላይ የቫይረሱ ተጠቂዎችን ሪፖርት እያደረገች ትገኛለች፡፡የቫይረሱን የስርጭት መጠን ለመቀነስ በሚል እስከ ወርሃ ሰኔ ማብቂያ እንቅስቃሴ የሚከለክለዉ መመሪያ ባለበት እንዲቀጥል የፔሩ መንግስት ትዕዛዝ አሳልፏል፡፡

በላቲን አሜሪካ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የሚገኝ ሲሆን በቀጠናዉ ብራዚል፣ፔሩና ቺሊ ይበልጥ ተጎጂ ሆነዋል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *