መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 11፤2012-ቻይና በአዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ልትገነባ ነዉ

የቻይና አፍሪካ ጉባዔ የኮቪድ 19 ቀዉስ አስመልክቶ በትላንትናዉ እለት በተካሄደዉ ስብሰባ ቻይና በአዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ እንደምትገነባ አስታወቀች፡፡

የቻይናዉ ፕሬዝዳንት ዢ ጂፒንግ እንደተናገሩት ቻይና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ከአለም የጤና ድርጅት እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመስራት ለአፍሪካ ድጋፍ ማድረጓን እንደምትቀጥል አስታዉቀዋል፡፡

ቻይና ወለድ አልባ ብድርን እስከ 2020 ባለዉ የጊዜ ገደብ ለአፍሪካ ሀገራት እንደምትሰርዝም ይፋ አድርጋለች፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *