መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 11፤2012-የፍቅረኛዬን ከንፈር በመሳሜ ኧርፒስ በተባለዉ ቫይረስ ተይዣለዉ ያለዉ አፍቃሪ 160ሺ የአሜሪካን ዶላር ካሳ ጠየቀ

የ45 ዓመቱ እንግሊዛዊዉ ሰዉ ማርቲን ኮንዌይ የለንደን ከተማ ነዋሪ ሲሆን ሜት አፕ ዶት ኮም በተባለ የፍቅረኛ አጣማሪ ዌብሳይት የፍቅር ግንኙነት ይጀምራል፡፡ላቭሌስ ከተባለች ሴት ጋር የጀመረዉ ፍቅር በኦንላይን ብቻ ሳይገታ በአካል ይገናኛሉ፡፡

የፍቅር ቀጠሮ በያዙበት እለት ታዲያ ጥሩ እራት ተመግበዉ ማርቲን ኮንዌይ እና ላቭሌስ ሌሊቱን በጋራ ያሳልፋሉ፡፡በዛች ለሊት ከንፈር ለከንፈር መሳሳማችን ግን መዘዝ አምጥቶብኛል ሲል አፍቃሪዉ ዘግይቶ ተናግሯል፡፡

ከእርሷ ጋር ካሳለፍኩበት እለት ማግስት አንስቶ የጉንፋን ስሜት ነበረኝ፣ከንፈሬ ላይ ህመም አለ በተለይ ስመገብ ተቸግሬያለዉ ሲል ያሳውቃል፡፡ኧርፒስ በተባለዉ ቫይረስ ተጠቂ መሆኗን ልትነግረኝ ይገባል ይህንን ባለማድረጓ ደግሞ 160ሺ የአሜሪካን ዶላር ካሳ ትክፈለኝ ሲል ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስዶታል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *