መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 11፤2012-ጅቡቲና ኬንያ ለጸጥታዉ ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነት ለመመረጥ እየተፎካከሩ ይገኛል

በዛሬዉ እለት ሁለቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ጅቡቲና ኬንያ ለጸጥታዉ ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ለመሆን በሚያደርጉት ፉክክር ላይ ድምጽ ይሰጣል፡፡አፍሪካን ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት በምክር ቤቱ በመወከል ከሁለቱ ሀገራት አንዳቸዉ ተሳትፎ ይኖራቸዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በትላንትናዉ እለት ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የምክር ቤቱ ተለዋጭ አባል ሀገራትን ሲመርጥ ዉለዋል፡፡አፍሪካ ካላት ሶስት መቀመጫ መካከል ሀለቱ በኒጀርና ቱኒዚያ መያዙ ከወዲሁ ተረጋግጧል፡፡

ኬንያ እና ጅቡቲ ለምክርቤቱ ማግኘት ካለባቸዉ ድምጽ 2/3ኛዉን ማግኘት ባለመቻላቸዉ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ በዛሬው እለት ቀጥሎ ይዉላል፡፡በትላንትናዉ የድምጽ አሰጣጥ ኬንያ 113 ድምጽ ስታገኝ ጅቡቲ 78 መቀመጫ አግኝታለች፡፡

ፈረንሳይኛ ተናጋሪዋ ጅቡቲ ከእንግሊዘኛ ተናጋሪዋ ኬንያ ጋር እያደረጉት ባለዉ ፉክክር ሀገራቱ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ህንድ፣ሜክሲኮ፣ኖርዌይ፣አየርላንድ የጸጥታዉ ምክር ቤ ተለዋጭ ወንበርን ማግኘት የቻሉ ሲሆን ካናዳ በድጋሚ ይህንን ማሳካት ሳይቻላት ቀርቷል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *