መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 12፤2012እዉቁ የአሜሪካ አሳታሚ ዋርነር ሪከርድስ በጥቁሮች ተቃዉሞ ዙርያ ያቀነቀነዉን የ12 ዓመት ታዳጊ አስፈረመ

የ12 ዓመቱ ታዳጊ ኬንድሮን ብራይንት የሚባል ሲሆን በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ማግስት ያቀነቀነዉ ዜማ ከፍተኛ ተደማጭነትን አግኝቶለታል፡፡ታዳጊዉ ወጣት ጥቁር አሜሪካዊ መሆን ዉስጥ ያለዉን ፍራቻ በዜማዉ አቀንቅኗል፡፡

I Just Wanna Live የተሰኘ መጠሪያ ያለዉን ዜማ በታዳጊዉ ወላጅ እናት ግጥሙ ተሰናድቷል፡፡በኢንስታግራም ላይ ከ3 ሚሊየን ጊዜ በላይ ተወዳጅነትን ያገኘ ሲሆን የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ፣የቅርጫት ኳስ የምንግዜም ኮከብ ተጫዋች ሊብሮን ጀምስ፣ጃኒት ጃክሰን አድናቆታቸዉን ለታዳጊዉ ቸረዋል፡፡

ግጥሙን የጻፈችዉ የታዳጊዉ እናት ጆንኔት ብራይንት የጆርጅ ፍሎይድ የግፍ ግድያ ከተመለከትኩ በኃላ መኖር ፈራዉ ምክንያቱን እኔም ጥቁር ባል፣ጥቁር ወንድሞች፣ጥቁር አጎትና ጓደኞች አሉኝ ስትል ተናግራለች፡፡

ዋርነር ሪከርድስ የተሰኘዉ አሳታሚ የሚገኘዉን ገቢ በዘር ቀለማቸዉ የተነሳ መድሎ ለሚደርስባቸዉ ይሆናል ሲል አሳዉቋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *