መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 12፤2012-በማሊ ፕሬዝዳንቱ ስልጣን እንዲለቁ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በማሊ መዲና ባማኮ አደባባይ የነፃነት አደባባይ በመገኘት ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ኬታ ስልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል።ፕሬዝዳንቱ የጂሃዲስቶችን ጥቃት መከላከል አልቻሉም በሚል ተወቅሰዋል።

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት መሪ በማሊ ያለው ሙስና ሊያበቃ እንደሚገባ በሰልፉ ላይ በመገኘት ጥሪ አስተላልፈዋል።የማሊ መንግስት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማሻሻያ ማድረግ እንዳለበትም ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንቱ ከዛሬው ተቃውሞ አስቀድመው በሳምንቱ መጀመሪያ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት የተካተቱበት የአንድነት መንግስት እንደሚመሰርቱ ቃል ገብተው ነበር።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *