መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 12፤2012-ቻይና በቁጥጥር ስር አዉላቻቸዉ የነበሩ 10 የህንድ ወታደሮችን መልቀቋ ተሰማ

የሂንዱ ጋዜጣ ከህንድ የጦር ምንጮቼ አገኘሁት ብሎ ለንባብ እንዳበቃዉ ከሆነ በቻይና እጅ ስር ከነበሩ ወታደሮች መካከል 10ሩ ነጻ መደረጋቸዉን ጽፏል፡፡አንድ ሌተናል ጀነራልና ሶስት ተጨማሪ ከፍተኛ የጦሩ ሀላፊዎች እንዳሉበት ይፋ ተደርጓል፡፡

የህንድ መንግስት በመረጃዉ ዙርያ ዝምታን መርጧል፡፡በጋላዋን ስምጥሸለቆ በነበረዉ የቻይናና ህንድ ወታደሮች የተኩስ ልዉዉጥ ህንድ ቢያንስ 20 ወታደሮቿን ህይወት ስትቀማ 76 ወታደሮች ደግሞ ቆስለዋል፡፡በቻይና በኩል ስለደረሰዉ ጉዳት ግን እስካሁን ይፋ አልተደረገም፡፡

ሁለቱ ሀገራት ቀድሞ ጸብ ጫሪ ተኩስ የከፈተዉን በተመለከተ አንዳቸዉ ሌላቸዉን መወንጀል ቀጥለዋል፡፡ሁለቱ ሀገራት ከ45 ዓመታት ወዲህ ደም አፋሳሽ የተኩስ ልዉዉጥ ሲያደርጉ የአሁኑ የመጀመሪያዉ ነዉ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *