መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 12፤2012-የሆንዱራስ ፕሬዝዳንት በመልካም የጤንነት ደረጃ ላይ ይገኛሉ ተባለ

የሆንዱራስ ፕሬዝዳንት ጁአን ሀርናንዴዝ የኮሮና ቫይረስ ህክምናቸዉን መከታተል የጀመሩ ሲሆን በመልካም የጤና ደረጃ ላይ እንደሚገኙ በወታደራዊ ሆስፒታል ዶ/ር ሲሳር ካራስኮ ተናገሩ፡፡በሆስፒታሉ ባለፉት ሁለት ቀናት ህክምናቸዉን መከታተላቸዉ ተገልጿል፡፡

ፕሬዝዳንት ጁአን ሀርናንዴዝ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉን ተከትሎ የመተንፈስ እክል እንዳላጋጠማቸው የተናገሩት ዶ/ር ካራስካ ሆኖም ግን በእግሮቻቸዉ ለመንቀሳቀስ እንደቸገራቸዉ ግልጽ አድርገዋል፡፡ለምን ያህል ቀናት በሆስፒታሉ እንደሚቆዩ አልተገለጸም፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *