መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 12፤2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ የህንድ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ ለኮሮና ቫይረስ የመከላከያ ጋሻው ዮጋ ነው ሲሉ ተናገሩ።የፊታችን እሁድ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የዮጋ ቀንን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት የበሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል ሲሉ ተደምጠዋል።

~ ስዊዘርላንድ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ እስከ 1ሺ ሰው መሰብሰብ የሚያስችለውን መመሪያ ትፈቅዳለች።

~ ታይላንድ ባለፉት 25 ቀናት በሀገር ውስጥ የተዛመተ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ አለማግኘቷን አስታወቀች።ከሳዑዲ በመጡ ዜጎች ላይ ብቻ ቫይረሱ መገኘቱን ይፋ አድርጋለች።3,146 ተጠቂዎች የነበሩባት ታይላንድ 3,008ቱ ሲያገግሙ የ58 ሰዎች ህይወት አልፏል።

~ በጣልያን የኮሮና ቫይረስ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አስቀድሞ በታህሳስ አጋማሽ መኖሩን በሚላን እና ቱሪን ከተሞች ከተወሰደ ናሙና ማረጋገጥ ተቻለ።

~ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በአሜሪካ ግዛቶች ፍሎሪዳ፣በሰሜናዊና ደቡባዊ ካሮላይና፣አሪዞና እየጨመረ በመሆኑ አፕል በጊዜያዊነት ሱቆቹ በአራቱ ግዛቶች ሊዘጋ ነው።

~ በሳዑዲ አረቢያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ150ሺ ሲበልጥ የሟቾች ቁጥር 1,184 ደርሷል።ኳታር በበኩሏ የቫይረሱ ተጠቂዎች 85ሺ መድረሱን ይፋ ያደረገች ሲሆን 1,021 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

~ ዩኑሴፍ 10ሺ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያን ለየመን መላኩን አሳወቀ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *