መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 12፤2012-የኖቤል የሰላም አሸናፊዋ ማላላ የሱፋይዝ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተቀበለች።

በሴቶች የትምህርት ዘመቻ ላይ የምትታወቀው ማላላ የሱፋይዝ 11 ዓመት ታዳጊ ሳለች በፓኪስታን በታሊባን አገዛዝ ስር ሆኖ ህይወት ምን እንደምትመስል ለቢቢሲ የፃፈችው ንባብ ከፍተኛ ተቀባይነት አስገኝቶላት ነበር።

ሆኖም በፓኪስታን ሳለች በታሊባን ታጣቂ ጭንቅላቷን በሽጉጥ ተመታ በፓኪስታን እና በእንግሊዝ በተደረገላት ተከታታይ ህክምና ህይወቷ ሊተርፍ ችሏል።

ከዚያ ወዲህ ሴቶች እንዲማሩ ባደረገችው ተሳትፎ በ17 ዓመቷ የሰላም የኖቤል ሽልማትን እንድታገኝ አስችሏታል።አሁን ላይ 22ኛ ዓመቷን ይዛለች።

ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ትምህርቷን ማጠናቀቋን ተከትሎ የህፃናት አድን ፈንድ(ዩኒሴፍ) እና የሆሊውድና ቦሊውድ ፈርጧ ፕሪያንካ ቾፕራ ለማላላ የእንኳን ደስ ያለሽ ሲሉ መልዕክት ካስተላለፉት መካከል ናቸው።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *