መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 12፤2012-ፌስቡክ የዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ዘመቻ ማስታወቂያን ከፌስቡክ ላይ እንዲነሳ አደረገ

ፈስቡክ የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ማስታወቂያ ላይ የናዚ ጀርመን ምልክት መኖሩን ተከትሎ ከኩባንያዉ ፖሊሲ ጋር የሚቃረን ነዉ በሚል ማስታወቂያዉን ከማህበራዊ ገጹ ትስስር እንዲወርድ አድርጓል፡፡ፌስቡክ የደህንነት ፖሊሲ ሀላፊ ናትናኤል ግሊቸር እንደተናገሩት ከሆነ የተደራጀ የጥላቻ ቡድኖች መልዕክትና የጥላቻ ርዕዮተ ዓለም ቅስቀሳ አናስተናግድም ብለዋል፡፡

ማስታወቂያ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በምክትላቸዉ ማይክ ፔንስ ከተጫነ 24 ሰዓታት ከቆየ እንዲሁም በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ተመልካች ካገኘ በኃላ እንዲነሳ ተደርጓል፡፡

ምልክቱ የተገለበጠ ቀይ ሶስት ማዕዘን ሲሆን ጸረ ፋሽስት የሚባሉት አንቲፋ የተሰኙት ቡድኖች የሚጠቀሙበት ነዉ፡፡የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቃል አቀባይ የሆኑት ቲም ሙርታዉግ እንደተናገሩት አንቲፋን ለመወከል የተደረገ ነዉ ብለዋል፡፡

ቲም ሙርታዉግ ጨምረዉ ፌስቡክ ራሱ የተገለበጠ ቀይ ሶስት ማዕዘን ኢሞጂ ጥቅም ላይ ያዉላል ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ፕሬዝዳንት ትራምፕ አንቲፋ የተሰኘዉን ቡድን የጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ተከትሎ በሀገሪቱ ለተነሳዉ ቀዉስ መክሰሳቸዉ አይዘነጋም፡፡

አንቲፋ የተሰኘዉ ቡድን ስደተኛ ጠል እና ጠንካራ ብሄርተኝነትን የሚያቀነቅን ነዉ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *