የሆንዱራስ ፕሬዝዳንት ጁአን ሀርናንዴዝ የኮሮና ቫይረስ ህክምናቸዉን መከታተል የጀመሩ ሲሆን በመልካም የጤና ደረጃ ላይ እንደሚገኙ በወታደራዊ ሆስፒታል ዶ/ር ሲሳር ካራስኮ ተናገሩ፡፡በሆስፒታሉ ባለፉት ሁለት ቀናት ህክምናቸዉን መከታተላቸዉ ተገልጿል፡፡
ፕሬዝዳንት ጁአን ሀርናንዴዝ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉን ተከትሎ የመተንፈስ እክል እንዳላጋጠማቸው የተናገሩት ዶ/ር ካራስካ ሆኖም ግን በእግሮቻቸዉ ለመንቀሳቀስ እንደቸገራቸዉ ግልጽ አድርገዋል፡፡ለምን ያህል ቀናት በሆስፒታሉ እንደሚቆዩ አልተገለጸም፡፡
በሚኪያስ ጸጋዬ