መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 15፤2012-በማላዊ በነገው እለት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ይካሄዳል

በግንቦት 2019 ዓመት በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፕሬዝዳንት ፒተር ሙታሪካ ማሸነፋቸው በምርጫ ኮሚሽን መታወጁ ይታወሳል።የምርጫ ኮሚሽኑ ሙታሪካን አሸናፊ ቢያደርግም ተቀዋሚዎች ጉዳዩን ወደ ህገመንግስት ፍርድ ቤት በመውሰድ ምርጫው እንዲደገም ሆኗል።

በወርሃ ታህሳስ ፍርድ ቤቱ በ150 ቀናት ውስጥ ማላዊ ምርጫ እንድታደርግ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ተከትሎ በነገው እለት የቁርጥ ቀን ሆኗል።ከ6 ሚሊየን በላይ መራጮች ከሶስት ሺ በላይ በሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ድምፅ ይሰጣሉ።

ፕሬዝዳንት ፒተር ሙታሪካ በመሰረተ ልማት ግንባታ እና የግሽበት መጠን በማስተካከል የሚመሰገኑ ቢሆንም አስተዳደራቸው በሙስና ይተቻል።በነገው ምርጫ ሰፊ የማሸነፍ ግምት ከተሰጣቸው ተቀናቃኛቸው ዶ/ር ላዙራስ ቻክዊራ ጋር ይፋለማሉ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *