መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 15፤2012-ባለፈው ዓመት ሕይወታቸው ያለፉ የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች የመታሰቢያ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው።

በሥነ ሥርዓቱ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ሌሎች የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

መርሀ ግብሩ ባለፈው ዓመት 2011 በሰኔ 15 በክልሉ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር ሕይወታቸውን ላጡ የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የፀጥታ ኃይሎች መታሰቢያ ነው።

በርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት ግቢ ለመሪዎቹ የመታሰቢያ ሃውልት መሠረት ተቀምጧል፡፡

የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ዝክረ ሰማዕታት የችግኝ ተከላ መርሀ ግብርም እየሄዱ ነው።

በችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ፣ የክልሉ
ምክር ቤት አፊ ጉባኤ ወርቅ ሰሞ ማሞ፣ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ችግኝ ተክለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር 5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዷል፤ በአማራ ክልል ደግሞ 1 ነጥብ 75 ቢሊዮን ችግኝ የመትከል ሥራው ተጀምሯል፡፡

ከእነዚህም 165 ሚሊዮን ችግኞች በአማራ ክልል ከተሞች የመትከል መርሀ ግብር መያዙ
ይታወሳል።

አብመድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *