መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 15፤2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ በፊልምና በቴሌቪዥን ዘርፍ ምርጦችን የሚሸልመው የጎልደን ግሎብ አዋርድ ወደ የካቲት መጨረሻ ተዘዋወረ።ከአንድ ሳምንት በፊት የኦስካር የሽልማት ስነ ስርራት በቫይረሱ የተነሳ መዘዋወሩ ይታወሳል።

~ በኔዘርላንድ ከመጋቢት ወር በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፉት 24 ሰዓት በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ሞት አለመመዝገቡ ይፋ ተደረገ።በኔዘርላንድ በአጠቃላይ የተመዘገበው የሞት መጠን 6,090 ነው።

~ ስፔን በተያዘው ሳምንት ከአውሮጳ ሀገራት ውጪ ለሚገኙ ቱሪስቶች በሯን ክፍት እንደምታደርግ አስታወቀች።የ28,323 ሰዎች ህልፈት በተመዘገበባት ስፔን የቫይረሱ የስርጭት መጠን አሁን ላይ እየቀነሰ ይገኛል።

~ በስኮትላንድ ባርና ሬስቶራንት የሚጠቀሙ ሰዎች ስለ ራሳቸው የሚገልፅ መረጃ እና አድራሻቸውን የመስጠት ግዴታ እንዳለባቸው ስኮትላንድ አስታወቀች።

~ በዩናይትድ ኪንግደም ከመጋቢት 15 ወዲህ ዝቅተኛ የተባለው የሞት መጠን ባለፉት 24 ሰዓት ተመዘገበ።ባለፉት 24 ሰዓት 15 ሞት ብቻ የተመዘገበ ሲሆን አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 42,647 ደርሷል።

~ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ አስቸጋሪ ውሳኔ እና አስቸጋሪ ቀናቶች ከፊታችን አለ ሲሉ ተናገሩ።
በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና እያሳደረ መሆኑን ገልፀዋል።

~ ሀይማኖታዊ ክንውኖች በስፋት መደረጋቸው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዲጨምር አስተዋጾ ማድረጋቸውን የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *