መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 17፤2012-ኒጀር ከጦር መሳሪያ ግዢ ጋር በተያያዘ 50 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የምዝበራ ቅሌት እንደተፈፀመ አስታወቀች

የኒጀር ጠቅላይ አቃቢ ህግ እንዳስታወቀው ከጦር መሳሪያ ግዢ ጋር በተያያዘ 50ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የገባበት አልታወቀም ብሏል፡፡

በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ በተደረገ ኦዲት ክፍያ የተፈፀመባቸው የተለያዩ ቁሳቁሶች ቢኖርም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አለመረከቡን ጠቅላይ አቃቢ ህግ ማማን ሳያቦዩ ተናግረዋል፡፡ የሀሰተኛ ሰነድ እና አሻጥር ስለመኖሩም አረጋግጠናል ብለዋል፡፡

በጂሃዲስቶች ጥቃት ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለች የምትገኘው ኒጀር የጦር ሃይሉ ጥቃቱን መከላከል ያልቻለው በውስጡ ባለው የሙስና ነቀርሳ እንደሆነም እየተነገረ ይገኛል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *