የኒጀር ጠቅላይ አቃቢ ህግ እንዳስታወቀው ከጦር መሳሪያ ግዢ ጋር በተያያዘ 50ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የገባበት አልታወቀም ብሏል፡፡
በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ በተደረገ ኦዲት ክፍያ የተፈፀመባቸው የተለያዩ ቁሳቁሶች ቢኖርም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አለመረከቡን ጠቅላይ አቃቢ ህግ ማማን ሳያቦዩ ተናግረዋል፡፡ የሀሰተኛ ሰነድ እና አሻጥር ስለመኖሩም አረጋግጠናል ብለዋል፡፡
በጂሃዲስቶች ጥቃት ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለች የምትገኘው ኒጀር የጦር ሃይሉ ጥቃቱን መከላከል ያልቻለው በውስጡ ባለው የሙስና ነቀርሳ እንደሆነም እየተነገረ ይገኛል፡፡
በስምኦን ደረጄ