መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 18፣2012-ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከኢቦላ ቫይረስ መሉ ለሙሉ ነፃ መሆኗ ታወጀ

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ባለፉት 23 ወራት የኢቦላ ቫይረስ መቀስቀሱን ተከትሎ 3,463 ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ የ2,280 ሰዎች ህይወት አልፏል።ባለፉት 42 ቀናቶች በቫይረሱ የተጠቃ አንድም ሰው አልተገኘም።

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ቫይረሱን የመቆጣጠር ሂደቷ ፈታኝ የነበረ ሲሆን በታጣቂ ቡድኖች ከ420 በላይ የጤና ተቋማት ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል።በሀገሪቱ ኢቦል ከ1970ዎቹ አንስቶ ለ11 ጊዜያት ያህል ተቀስቅሷል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *