መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 18፤2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ የካዛኪስታን የጤና ሚንስትር የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ።ሚንስትሩ የልዚሃን ብሪታኖቪ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸውን ገልፀው እንደነበር አይዘነጋ።አሁን ላይ ቫይረሱን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የማልችልበት ደረጃ ላይ እገኛለሁ ሲሉ ተናግረዋል።

~ የፈረንሳይ ምልክት የሆነው የኤፍል ማማ ለጎብኚዎች ክፍት ተደረገ።ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ወዲህ ዘለግ ላለ ጊዜ ዝግ ሲደረግ የአሁኑ የመጀመሪያው ነው።እ.ኤ.አ በ1889 የማማው ግንባታ ክፍት መደረጉ ይታወሳል።ፈረንሳይ ከ29ሺ በላይ ዜጎቿን በቫይረሱ ተነጥቃለች።

~ በአሜሪካ ህዝብ በሚበዛባቸው ሶስት ግዛቶች የኮሮና ቫይረስ መዛመት ጨመረ።ከአሜሪካ ህዝብ 27 በመቶ የሚኖርባቸው ግዛቶች የሆኑት ፍሎሪዳ፣ቴክሳስና ካሊፎርኒያ ናቸው።

~ በገልፍ ሀገራት በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ዜጎች ቁጥር ከ400ሺ በላይ ሆነ።በሳዑዲ፣ኢምሬትስ፣ኩዌት እና ኦማን ከፍተኛ የስርጭት መጠን ተመዝግቧል።

~ በደቡብ አፍሪካ ምዕራባዊ ኬፕ ግዛት የሚገኙ መምህራን እና ወላጆች በኮሮና ቫይረስ ስጋት የተነሳ ክፍት የተደረጉ ትምህርት ቤቶች ይዘጉ ሲሉ ተቃውሞ አሰሙ።ከ300 በላይ የትምህርት ቤቶች ሰራተኞችና 61 ተማሪዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

~ በላቲን አሜሪን ሀገራት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር በሶስት እጥፍ መጨመሩን በፓን አሜሪካ የአለም የጤና ድርጅት ቢሮ አስታወቀ።

~ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የአደንዛዥ እፅ ተጠቃሚዎችን ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት ሊሆን ይችላል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአደንዛዥ እፅ እና ወንጀል መከላከል ተቋም አስታወቀ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *