መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 19፤2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ ህንድ የባቡር አገልግሎት ወደ ስራ እንዲገባ የሰጠችውን ፍቃድ መልሳ ከለከለች።በ24 ሰዓት ውስጥ ከ17ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸው ስጋት ፈጥሯል።ከ490ሺ በላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች ሲመዘገብ የ15,300 ሰዎች ህይወት አልፏል።

~ በአሜሪካ በየእለቱ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የሚደረግላቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 500ሺ እየተጠጋ ይገኛል።በየእለቱ በቫይረሱ ከሚጠቁ ሰዎች 50በመቶ ያህሉ እድሜያቸው ከ35 ዓመት በታች ነው።

~ የራሺያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከሁለት ወር በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ የቫይረሱ የስርጭት መጠን እየቀነሰ መምጣቱን አስታወቁ።ፈጣሪን እናመሰግናለን ያሉት ፑቲን እለታዊ የተጠቂዎች ቁጥር ከ7ሺ በታች ተመዝግቧል።በመላው ራሺያ 620ሺ ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ የ8,770 ሰዎች ህይወት አልፏል።

~ አስትራዜኔካ የተባለ መድሃኒት አቅራቢ ለኮሮና ቫይረስ የተሻለ የተባለውን የክትባት መድሃኒት ማቅረቡ ተሰማ።የአለም የጤና ድርጅት ከ200 በላይ የክትባት መድሃኒት እጩዎች ቀርበውለታል።

~ በአሜሪካ ሰሜን ካሊፎርኒያ በአንድ የቤተሰብ ግብዣ ላይ ከተሳተፉ ግለሰቦች 13ቱ በኮሮና ቫይረስ ተያዙ።

~ ደቡብ አፍሪካ ከሰኞ ጀምሮ ሲኒማ እና ቁማር መጫወቻ ቤቶችን ክፍት ልታደርግ ነው።ከ118ሺ በላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች ባሉባት ደቡብ አፍሪካ የ2,292 ሰዎች ህይወት አልፏል።

~ የእውቁ ቴኒስ ተጫዋች ኖቫክ ጆኮቪች አሰልጣኝ እና የቀድሞ የዊምብሌደን ሻምፒዮን ኢቫኒስቪክ በኮሮና ቫይረስ መጠቃቱ ተሰማ።ኖቫክ ጆኮቪች እና ባለቤቱ በቫይረሱ መያዛቸው አይዘነጋም።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *