መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 19፤2012-ናይክ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ከፍተኛ ኪሳራ እንዳጋጠመዉ አስታወቀ

የአለማችን ግዙፉ የስፖርት ትጥቅ አምራች የሆነዉ ናይክ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ የሽያጭ መቀዛቀዝ እንዳጋጠመዉ ይፋ አድርጓል፡፡ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ገቢዉ 38 በመቶ የቀነሰበት ናይክ 6.31 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር የትርፍ መቀዛቀዝ አጋጥሞታል፡፡የናይክ 90 በመቶ የሽያጭ መደብሮች በሰሜን አሜሪካ፣አዉሮጳ እና የደቡብ አሜሪካ ዝግ ተደርገዋል፡፡

????????በአሜሪካ በ24 ሰዓት ዉስጥ 2,430 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉ አለፈ

ባለፉት 24 ሰዓት በአሜረካ በኮሮና ቫይረስ ተጨማሪ 40,598 ሰዎች መጠቃታቸዉ ሲነገር የ2,430 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ይፋ እንዳደረገዉ በቫይረሱ ከ2.4 ሚሊየን በላይ ዜጎች ሲጠቁ የሟቾች ቁጥር 124,410 ደርሷል፡፡

በሜክሲኮ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ200ሺ በልጧል

????????የሜክሲኮ የጤና ሚንስቴር እንዳስታወቀዉ ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 6,104 ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ 736 ሞት ተመዝግቧል፡፡በሜክሲኮ በቫይረሱ 200,951 ዜጎች ሲጠቁ የሟቾች ቁጥር 25,060 ደርሷል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *