መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 19፤2012-”የሊጉ ሻምፒዮኞች ነን!” ሊቨርፑላውያን

የ 30 ዓመቱ ድርቅ ማብቃቱን ተከትሎ የሊቨርፑል ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ደስታቸውን እያጣጣሙ ይገኛል፡፡

ትናንት ምሽት በስታንፎርድ ብሪጅ ማንችስተር ሲቲ በቼልሲ 2ለ1 መሸነፉን ተከትሎ የሊጉ ሻምፒዮንነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

የጀርገን ክሎፕ ቡድን በ 31 ጨዋታዎች ሰባት ብቻ ነጥብ በመጣል ሰባት ጨዋታዎች እየቀሩ ሻምፒዮን መሆን ችለዋል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተቋርጦ የቆየው ሊጉ አዲሱንና ከ 30 ዓመታት በኋላ የዋንጫው ባለቤት መሆን ለቻለው ክለብ ክብር ሰጥቷል፡፡

የክብሩ ባለታሪኮችም ተከታዮች አስተያየቶች በትዊተር አካውንታቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

ቨርጅል ቫኝ ዳይክ ‹‹በስተመጨረሻም ለማለት በቃን! ከ 30 ዓመታት በኋላ ሊቨርፑል ክብሩን ተቀዳጅቷል››

አንድሪ ሮበርትሰን ‹‹የፈጣሪ ያለህ››

ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ ‹‹ብቻችሁን አትጓዙም››

ጄምስ ሚልነር ‹‹30 ዓመት ቀያዮቹ! እንደሰት። የዚህ ቡድንና የክለቡ አካል በመሆኔ ክብር ይሰማኛል››

ዴጃን ሎቨረን ‹‹96 ???? ❤️ ህልሜ እውን ሆኖል፡፡

ዋይናልደም ????????????

አድሪያን ሳን ሚጉዌል ‹‹የሊጉ ዋንጫ ብቻውን አይጓዝም›

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *