መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 19፤2012-የብሩንዲ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ፔሪ ኒኩሪንዚዛ የቀብር ስነስርዓት በዛሬዉ እለት ይፈጸማል

ለ15 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ ብሩንዲን የመሩት ፔሪ ኒኩሪንዚዛ በድንገተኛ የልብ ህመም በስልጣን ላይ እያሉ ህይወታቸዉ ማለፉን ተከትሎ በዛሬዉ እለት በብሩንዲ መዲና ኪቲጋ የቀብር ስነ ስርዓታቸዉ ይፈጸማል፡፡በኪቲጋ ብሄራዊ ስታዲየም አሸኛኘት ይደረጋል፡፡

ኒኩሪንዚዛ የአሩሻ ስምምነት ተፈርሞ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸዉ በፊት ኒኩሪንዚዛ በአማጺ ቡድን ዉስጥ ለስምንት ዓመታት ታግለዋል፡፡የብሩንዲ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዲያበቃ የሰሩ ሲሆን በስልጣን ዘመናቸዉ የመጀመሪያዎቹ አስር ዓመታት ዉጤታማ ስራ እንደሰሩ ይነገርላችዋል፡፡

በሰላም፣የብሩንዲ የደን ሽፍን እንዲጨምር በማድረግ(በቅጽል ስም ፕሬዝዳንት አቮካዶ እስከመባል ደርሰዉ ነበር)በርካታ ስራዎችን አከናዉነዋል፡፡ሆኖም ግን በ2015 ስልጣናቸዉን ህገ መንግስቱ ከሚፈቅደዉ ዉጪ ማራዘማቸዉ ያስከተለዉ ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 200ሺ ሰዎች ሀገር ጥለዉ እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *